ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለድርድር ባዘጋጁት አጀንዳ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው

(ኤፍ ቢ ሲ)- ኢህአዴግን ጨምሮ ሃገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለድርድር ባዘጋጁት አጀንዳ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው።

ድርድሩን እያደረጉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመደራደራያ አጀንዳዎቻቸውን ለድርድ አደራጅ ኮሚቴ አስገብተዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ፓርቲዎቹ ለድርድር የመረጧቸው አጀንዳዎች፥ ሙሉ በሙሉ መቅረቡን የሚገመግም የዝግ ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው።

ፓርቲዎቹ ውይይቱን ከጨረሱ በኋላ ባደራጁት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ አማካኝነት ስምምነት ላይ በደረሱባቸው ጉዳዮች ላይ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.