ህወሓት ዳግም ታሪክ እየሰራ ይሆን?

በህወሓት ታሪክ ውስጥ እጅግ ብዙ አስደማሚ ገድሎች ተሰርተዋል:: የድርጅቱ ድንቅ እሴት … ችግሮች ልክ እንደ ጎልያድ ገዝፈው ሲመጡ ምክንያት ፍለጋ ወደ ውጪ ሲያማትር አለመታየቱ ነው:: ድክመቶቹንም ሆነ መፍትሄዎቹን ወደ ውስጡ በመመልከት ይፈትሻል … ለዚህም ይሳካለታል::

መቀሌ ላይ የከተሙት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱም የያኔውን … የትግሉን ዘመን መንፈስ እያስቀጠሉ መሆኑን እየተሰማ ይገኛል:: እነ ታጋይ አሞራው … እነ ታጋይ ሸዊት … እነ ታጋይ ሃየሎምና ሌሎች የትግሉ ሰማዕታት ህወሓት ወደ ሀዲዱ መመለሱን ሲያዩ በጏዶቻቸው በመኩራት ከሰማየ ሰማያት ሲፈግጉ ይታየኛል::

ንስር አሞራ ልክ በአርባኛው አመቱ ያረጁ ጥፍሮቹንና ማንቁርቱን በአዲስ ቀይሮ በመታደስ ከፍ ብሎ መብረር እንደሚጀምረው ሁሉ ህወሓትም ይኸው በአርባኛው አመቱ ገደማ እራሱን በማደስ ሂደት ላይ ይገኛል::

ከወደ መቀሌ የሚሰማው ዜና አስደሳች ነው:: የሰሞኑ ፋሽን የሆነው “ህዝበኝነት” (cheap populism) ከመምረጥ ይልቅ እንደ የትጥቅ ዘመኑ ወቅት ህዝባዊነትን መርጧል:: የስብሰባቸው ግለቱም ያንን እንደሚያሳይ እየተነገረ ይገኛል:: ከስብሰባው መጠናቀቅ ቀጥሎ ውሳኔዎቹን የሚመጥኑ ስራዎች ለማየት እንጠብቃለን::

ክብር ለሰማዕታቱ!!

Leave A Reply

Your email address will not be published.