ሊጠናቀቅ አንድ ወር የቀረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊራዘም እንደሚችል መንግስት ፍንጭ ሰጠ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዳሉት በመንግስት ጥናት መሠረት 82 በመቶ የሚሆነው ህዝብ አዋጁ እንዲራዘም ይፈልጋል፡፡

በሌላ በኩል በክልሎች መካከል የሚካሄድ ግጭት እንዲባባስ ያደረጉና ያነሳሱ ሰዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የፌደራል መንግስት ወስኗል ብለዋል፡፡

ያየሰው ሽመልስ

 

የ2008/2009 ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሰፊ ምክንያት ሆኖ ተግባራዊ የሆነው የአስቸይ ጊዜ አዋጅ ለመጠናቀቅ አንድ ወር ቀርቶታል፡፡

በዚህ መሀል በሳምንቱ አጋማሽ የአዋጁ ኮማንድ ፖስት በሰጠው መግለጫ፣ የማስፈፀሚያ መመሪያው በከፊል መሻሻሉን ገልጿል፡፡

በዚህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተወሰኑ ጉዳዮች በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥራ እንዲከወኑ የሚያስችል ማሻሻያ ተደርጐበታል፡፡

ይሁን እንጂ ጠ/ሚ/ር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የመንግስታቸውን የግማሽ ዓመት ሥራ ክንውን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት አዋጁ ሊራዘም የሚችልበት እድል መኖሩን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

መስከረም 28 ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲራዘም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች አሉ፤ ጠ/ሚሩ እንደሚሉት፡፡

በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩ ግጭቶች፣ በአውራ ጐዳናዎች ላይ የሚደረገው ዝርፊያዎች፣ በጥቂት የት/ት ተቋማት የሚታዩ የረብሻ ምልክቶች የፀጥታ አካላት አሁንም በአንድ ዕዝ ሥር ሆነው እንዲሠረ የሚያስገድዱ አጋጣሚዋች ሆነዋል ተብሏል፡፡

በም/ቤቱ ከተነሱ ሌሎች ነጥቦች ውስጥ በክልሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን የተመለተው ጉዳይ ይጠቀሳል፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ በኤረሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራና በትግራይ መካከል የሚካሄዱ ግጭቶች መፍትሔያቸው ምንድን ነው የፌዴራል መንግስቱስ ጣልቃ ገብነት ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁት አቶ ኃይለማርያም ፣ በተለይ በሶሌና በኦሮሚያ ክልል የተነሳውንግጭት በአብነት በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተጥዋል፡፡

በክልሎች መካከል የሚካሄደው ደም አፋሳሽ ግጭት የሚላሳ/// የልዩ ኃይል ፖሊስ ነው ብለውታል፡፡

በኢትዮጵያ በዓለም ሆነ በመንግስት ዘርፍ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዋች ሲባል ዜጐች ይፈናቀላሉ፡፡ ለዚህ የሚሆን ካሳም እንደሚከፈል ይነገራል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ግን ከሰው በቂም አይደለም፡፡ አሉ ባይ ናቸ  ው፡፡ ከዚያም አለፍ ሲል የማይከፈላቸው ዜጐች ጠ/ሚ/ር ኃ/ማርያም ስሙን መጥቀስ አልፈልግም ያሉት አንድ ክልል ከ100 ሚሊዮን የሚልቅ ገንዘብ ለልማት ተነሺዎች ካሳ ብሎ ወስዶ የክልሉና የዞኑ መንግስት ሹማምንት በአንዳንዱ የጐሳ አባላት ጋር ተባብረው ተከፋፍለውታል፡፡ እናም መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች የሚነሱ ዜጐች ካሳ እንዱያኙ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ዘዴ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የካሳ አከፋፈል ሥርዓትን የሚከታተል ድርድት ይቋቋማል፡፡

ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ስለምትከተለው በፖሊሲ ማሻሻያ የተጠየቁት ጠሚኒስትሩ ከአሁን በፊት ወደትግራይ ክልል ባቀኑበት ወቅት ከተናገሩት ሀሳብ የለየ ነገር ያሉት የለም፡፡ለወትሮው በኤርትራ ላይ እየተተገበረ ያለውን ፖሊሲ የሚከልስ አዲስ ጥናት መጠናቀቁን ግን በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.