ሕወሓት አስቸኳ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

(ኢዜአ)- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/  አስቸኳይ ጉባኤ ትላንትበመቀሌ ከተማ  የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ተጀመረ።

በዝግ የተጀመረው አስቸኳይ ጉባኤ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ  ድርጅቱ ከትላንት በስትያ ማምሻውን  ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው ጽሁፍ ገለልጿል።

ኢትዮ – ኤርትራን አስመልክቶ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ድርጅቱ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው የሁለቱንም ሀገራት ህዝቦች ዘላቂ ጥቅምና አንድነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

ሕወሓት ትክክለኛ ባልሆኑ  ወሬዎች ህዝቡ እንዳይደናገር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ጉዳዩን በዝርዝር ከአባላቱና ከህዝቡ ጋር እንደሚወያይበትም አስታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.