መንግስት በየመን የባህር ዳርቻ በቅርቡ ህይወታቸውን ባጡ ኢትዮጵያዊያን ማዘኑን ገለፀ

(ኢዜአ)- የመንግስት ኮሙኑኬሽን ጉዳችዮች ፅ/ቤት በላከው መግለጫ መንግስት ባደረገው ማጣራት 100 ሰዎችን ጭና  ከሶማሊያ ቦሳሶ ተነስታ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በየመን ባህር ዳርቻ በደረሰባት አደጋ ሚያዚያ 29፣2010 ሰጥማ ከ60 በላይ  ኢትዮጵያዊያን ህይወት ማለፉንንና የደረሱበት አለመታወቁን ገልጿል፡፡

ጀልባዋ ከአቅሟ በላይ  ሰው በመጫኗ ነበር የመስመጥ አደጋ የገጠማት፡፡

ከአደጋው የተረፉ 39 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር የመን ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ድጋፍ በማግኘት ላይ መሆናቸውን መንግስት ገልጿል፡፡

መንግስት በውጭ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታና እስር ላይ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እያደረገ ባለበት ወቅት በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

ዜጎችን በተለያዩ ማማለያ ሀሳቦች በህገ ወጥ መንገድ  ወደ ሌሎች አገራት እንዲሄዱ የሚያርጉት ህገወጥ ደላሎች ለዚህ ተግባር ተጠያቂ በመሆናቸው በዚህ ድርጊት ላይ ተካፋይ የነበሩትን አካላት ተጠያቂ ለማድረግ መንግስት ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለጫው  አመልክቷል፡፡ ዜጎችም እነዚህን ወገኖች በማጋለጥ ረገድ የሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.