መገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊነታቸውን እንዲያሻሽሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አሳሰበ

EBC – የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ይፋ ባደረገው ጥናት የመንግስት መገናኛ ብዙሀን በሚያሰራጫቸው ይዘቶች ሚዛናዊነታቸውን እንዲያሻሽሉ አሳሰበ፡፡

በአገሪቱ 9 የመንግስት ወይንም ህዝብ መገናኛ ብዙሀን ላይ በተደረገ ጥናት በ8 ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ሀሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

ጥናቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በመካከለኛ ደረጃ ተደማጭ ናቸው ብለዋል፡፡

ለወቅታዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ትኩረት መስጠታቸው ክልላዊ ክስተቶችን መሸፈናቸውና አስተማሪ መርሀ ግብሮችን ማሰራጨታቸው በጥንካሬ ተዘርዝሯል፡፡ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸው ማደጉም በበጎ ጎኑ ተጠቅሷል፡፡

ነገር ግን መገናኛ ብዙሀኑ የሚዛናዊነት ችግር አለባቸው፤ የይዘት ድግግሞሽ ይበዛባቸዋል፤ የምርመራ ስራዎቻቸውም አነስተኛ ነው ተብሏል፡፡

የሚድያ ነፃነት፣ ያቀራረብ ሳቢ አለመሆንና የማስታወቂያዎች መብዛት በድክመት ተነስቷል፡፡

በጥናቱ መሰረት ከመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በቴሌቪዥንም በሬድዮም ኢቢሲ በተከታተሳዮች ብዛት ቀዳሚ ነው፡፡

የአማራ ቴሌቪዥንና የደቡብ ኤፍኤም100.9 ጣቢያዎ ደግሞ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል ብሏል ጥናቱ፡፡

ሁሉም የመገናኛ ብዙሀን ግን ልዩ ፍላጎት ላላቸው ህብረተሰብ በቂ ሽፋን የላቸውም ተብሏል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅፈት ቤት መገናኛ በብዙሀኑን ለመደገፍ ጥናቱ ግብአት ይሆናል ብለዋል፡፡

መገናኛ ብዙሀኑ ለሚዛናዊ አሰራርና ለምርመራ ተግባሮቻቸው ፅፈት ቤቱ ከለላ እሰጣለው ብሏል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.