ሩሲያ ለኢትዮጵያ አምባሳደር ግሩም አባይ ሽልማት አበረከተች

(ኢዜአ)- የሩሲያ መንግስት የኢትዮጵያ ልዩ መልክተኛና ባለ-ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለነበሩት አምባሳደር ግሩም አባይ የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ሽልማት አበረከተ።

በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴርጌ ላቭሮቭ ለአምባሳደር ግሩም የተሰጠው ዕውቅና የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር ባበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።

ሽልማቱንም ከአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካሂል ቦግዳኖቭ እጅ መቀበላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ መረጃውን አድርሶታል።

አምባሳደር ግሩም አባይ በአሁኑ ወቅት ከሩሲያ ወደ ቤልጂየም በመዛወር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

ከ120 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.