ሰበር ዜና: የሀገር ሀብት ዝርፊያ ማሳያ – በጥቂቱ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቀጣጥሎ ያለው የፀረ-ሙስና ትግል በጥልቀትም ሆነ በስፋት እንዲቀጥል ህዝባችን እየተናገረ ይገኛል። ልክ እንደ መዥገር ህዝቡን ተጣብተው፤ እሱን በማደህየት እራሳቸውን ብቻ የሚያበለፅጉ ሹመኞች፣ ባለሃብቶችና ደላሎቻቸው ፍርዳቸውን እንዲያገኙ የማይመኝ ኢትዮጵያዊ አይገኝም – ከሌባዎቹ በስተቀር!!!

ከእያንዳንዱ ሙስና ጀርባ ከሀገርና ከህዝብ ላይ የተሰረቀ ሃብት አለ። ከመንገዶች ጥራት መጉደል ጀርባ፤ ከፍትህ መዛባት ጉዳይ ጀርባ፣ ከፕሮጀክቶች ጥራት መጉደልና መዘግየት ጀርባ …. የሙስና እጅ አለ። ጉዳዩ የሙሰኞቹ አለአግባብ መበልፀግ ብቻ ሳይሆን ከሃብታቸው ጀርባ የምትደኸይ ምስኪን ሀገር መኖሯ ነው።

ሀገርና ህዝብ ምን ያህል እንደተዘረፈ ለማሳያ በቅርቡ በፀረ-ሙስና ሊከሰሱ ሲባል ለጥቂት ቀደም ብለው ከሀገር የሸሹት የሁለቱ ግለሰቦችን የሀብት ምንጭ እንመልከት። እነዚህ ግለሰቦች ከክሱ ቀደም ብለው እንዴት ከሀገር መውጣት ቻሉ የሚለው እራሱ ትልቅ ምርመራ የሚያሻው ቢሆንም ሀገር ቤት ጥለውት የወጡት ንብረትም በቢልዮን የሚገመት ነው። እነዚህም ንብረቶች አላግባብ መበልፀግ በሚል ክስ እገዳ እንደተጣለባቸው ይታወሳል። ምናልባትም አቃቤህግ ማስረጃዎቹን አቅርቦ ሊያስወርሳቸው የሚችላቸው ናቸው።

በዛሬው ጦማር የቀረቡት ማስረጃዎች ባለ አምስት ኮከቡ የኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት የሆነው የአቶ ገምሹ በየነና የአስር ኮንስትራክሽን ባለቤት የሆነው የአቶ የማነ አብርሃ ጉዳይ ነው። (አቶ ገምሹ በየነም የትልቅ ኮንስትራክሽን ባለቤት ናቸው።)

ከፍርድቤት አካባቢ ያገኘነው ማስረጃ እንደሚያሳየው ሁለቱም ግለሰቦች ተራ የመንግስት ተቀጣሪ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን፤ ልክ ስራቸውን ለቀው ሲወጡ በአንድ ለሊት ሚልዮን ብሮች ያሏቸው ድርጅቶች ባለቤት መሆናቸውን ነው።

 

የአስር ኮንስትራክሽን ባለቤት የሆኑት አቶ የማነ አብርሃ

በአ/አበባ መንገዶች ባለስልጣን እስከ ሚያዝያ 1996 ዓም ድረስ ወርሃዊ ደሞዛቸው ብር 3,083 ብቻ ነበር።

ይህኚው ግለሰብ ሀምሌ 30/2000 ዓም ላይ ከአ/አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት ስራቸው ሲያቆሙ ወርሃዊ ደሞዛቸው ብር 3,946 ነበር።

ይህኝው ግለሰብ ግን ከአራት ወራት ቆይታ በሁዋላ በ 14 ሚልዮን ብር የግል ድርጅታቸውን መሰረቱ። ዛሬ ላይ የግለሰቡ ንብረት ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ መሆኑ ይታወቃል።

(CLICK ON THE IMAGE TO ENLARGE)

የገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ድርጅትና ባለ አምስት ኮከቡ የኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ገምሹ በየነ  

በኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 2/1987 – መጋቢት 30/1988 በጉልበት ሰራተኛነት ወርሃዊ ደሞዝ 50.00 ብር ይከፈላቸው የነበሩ ናቸው። ይህኚ ግለሰብ መስሪያ ቤቱን በገዛ ፈቃዳቸው እ.አ.አ. መስከረም 1/1999 ሲለቁ የማሽን ኦፕሬተር በመሆን ወርሃዊ ደሞዛቸው 472.00 ብር ብቻ ነበር።

ግለሰቡ ስራ ካቆሙ ሶስት አመት ልዩነት ውስጥ በ 741,987.875.00 ብር የግላቸው ድርጅትን መመስረታቸውን ሰነዶች ያሳያሉ። በአሁኑ ወቅት የግለሰቡ ሀብት በቢልየኖች የሚገመት ነው።

(CLICK ON THE IMAGES TO ENLARGE)

Leave A Reply

Your email address will not be published.