ሰበር ዜና!

መንግስት በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ጠርጥሮ 34 የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን፣ ባለሀብቶችንና ደላሎችን በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በፌዴራልና በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፣ በኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በተለያየ የኃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 26ቱ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

ሰባቱ የግል ባለሀብቶት ሲሆኑ አንዱ ደላላ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሁሉም በፍ/ቤት የማዘዣ ትዕዛዝ ቤታቸው እንዲበረበር ከተደረገ በኋላ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ብርና በብዙ ሺህዎች የተቆጠረ ዩሮና ዶላር ተገኝቶባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሥራ እንደቀጠለ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.