ሳዑዲ አረቢያ 2,800 የሠለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ልትቀበል ነው

የሳውዲአረቢያን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ የጠቀሰው ሳውዲ ጋዜት የዜና ምንጭ ኢትዮጵያዊያኑ ሰራተኞች በመጪዎቹ 2 ወራት ወደሀገሪቱ ገብተው ይሰራሉ ብሏል፡፡

እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ስራ ፈላጊዎችም በሀገራቸው ለሚሰማሩበት ስራ በቂ ስልጠና አግኝተው ወደሳውዲ እንደሚገቡ ዘገባው ገልጿል፡፡ የሳውዲ መንግስት በነዚህ ሰራተኞች ስምሪት ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከመግባባት ላይ መድረሱን መግለጫው ይጠቅሳል፡፡

በቅርብ ጊዜያት ሳውዲ አረቢያ ሰነድ አልባ ናቸው ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያን ከሀገር ስታስወጣ ቆይታለች፡፡ ሀገሪቱ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ሙሉለሙሉ ሀገር የሚለቁበትን ቀነገደብም ማስቀመቷ አይዘነጋም፡፡

አሁን ላይ በቀጣይ ሁለት ወራት ስልጠና አግኝተው በህጋዊ መንገድ በሳውዲ ይሰማራሉ የተባሉት ኢትዮጵያዊያን በወር 800 የሳውዲ ሪያል የደሞዝ ተመን እንደወጣላቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.