ቀንዳም ከብቶች በረቱን እያመሱት ነው! የጥሞና መፍትሔ ይፈለጋል!

(በኡስማን ሰዒድ) አሁን ኢህአዴግ ታሟል፡፡ ህመሙ ፅኑ ህመም ነው! ከራሱ አልፎ ለአገር የተረፈ ፅኑ ወረርሽኝ  ነው!  በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ከእንቅልፍ ስለሚያባንናቸው ስጋት ሲናገሩ ፡በዚህች አገር መታየት የጀመረ ብርሃን የሆነ አካል ከሆነ ቦታ በሚፈፅመው ስህተት እንደሚበላሽ  ሲያስቡት መሆኑን ገልፀው ነበር፡፡  አሁን ብልሽቱ ተከስቷል፡፡ ከእንቅልፉ የሚባንንም ፡ ወዴት እየሄድን ነው የሚልም ወይ ጠፍቷል ወይ ሰሚ አጥቷል፡፡ ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን ያለው እድል  በጣም ጠባብ ሆኗል፡፡ በብዙ መለኮታዊ እና ታሪካዊ ማጣቀሻ አገር እንደማይፈርስ የሚከራከር  ቢኖርም  የኤርትራ ልምድ ብዙ እንዳንል ያደርገናል፡፡ ስለዚህ  ጥሞና ያስፈልጋል!

በጥቂት ፖለቲከኞች ፍላጎት የተነሳ የየራሱን ትንንሽ መንግስት የመመስረት ዓላማ ያለው ክልልና ብሔር ተኮር ጠባብ አመራር ኢህአዴግን ወሮታል፡፡ ፓርላማው ህግ አያከብርም አያስከብርም፤ ስራ አስፈፃሚው ህግ አያከብርም አያስከብርም፤ የፍትህ አካሉ ተራ መጠቀሚያ  ነው፡፡ አሁን አገር ከማዳን ይልቅ፡ ቡድን ማዳን ቁልፍ ስራ የሆነበት አመራር የኢትዮጵያ ባለቤት ሆኗል፡፡  ቀንዳም  ከብቶች ጋጡን (በረቱን) እያመሱት ነው፡፡ ሁሉም ጭድና ገለባ ለእኛ ብቻ የሚሉ ቀንዳሞች የበላይነት ይዘዋል! ጂቲፒ 2 ምንድን ነው? በሉ ፤ ጅቲፒ 2 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው! ጅቲፒ 2 የሰላም ማስከበር ነው! ስለዚህ  ጥሞና ያስፈልጋል! የት ይደርሳል የተባለው…..

አገር የማዳን ሚና ያለው ጥሞና አስፈላጊ ሆኗል፡፡ የትኛው አካል ፤ መቼ መቼ ፤ ምን ዓይነት ውሳኔዎችን መወሰን ሲጀምር፤ለምን ነገሮች መበላሸት እንደጀመሩ መፍትሔ ለመስጠት በጥሞና ማሰብና በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ቀንዳም ከብቶች ባሉበት በረት መቀየር አልያም በረቱን ሰንጥቆ መለያየት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ቀንድ ለመቁረጥ አስቸጋሪ ሁኔታ መኖሩ ግልፅ ነው፡፡ መፍትሔው በረት የሚያምሱ ከብቶችን ሳይቀደሙ ወደቄራ መላክ ነው!! ሳይቀደሙ መቅደም !! በሬና ላሞች ከተመቱ ወይፈንና ጊደሮች ይበተናሉ! ያኔ አገር ይድናል፡፡ አሁን ፍፁም አስፈሪና አሳፋሪ ኢህአዴግነት እየታየ ነው፡፡ ኪራይ አዳኞች የበላይነታቸውን ተጠቅመው የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ነው! ስለዚህ የጥሞና መፍትሔ ያስፈልጋል!

ቀንዳም ከብቶች በረቱን እያመሱት ነው! የጥሞና መፍትሔ ይፈለጋል!

አሁን ኢህአዴግ ታሟል፡፡ ህመሙ ፅኑ ህመም ነው! ከራሱ አልፎ ለአገር የተረፈ ፅኑ ወረርሽኝ  ነው!  በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ከእንቅልፍ ስለሚያባንናቸው ስጋት ሲናገሩ ፡በዚህች አገር መታየት የጀመረ ብርሃን የሆነ አካል ከሆነ ቦታ በሚፈፅመው ስህተት እንደሚበላሽ  ሲያስቡት መሆኑን ገልፀው ነበር፡፡  አሁን ብልሽቱ ተከስቷል፡፡ ከእንቅልፉ የሚባንንም ፡ ወዴት እየሄድን ነው የሚልም ወይ ጠፍቷል ወይ ሰሚ አጥቷል፡፡ ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን ያለው እድል  በጣም ጠባብ ሆኗል፡፡ በብዙ መለኮታዊ እና ታሪካዊ ማጣቀሻ አገር እንደማይፈርስ የሚከራከር  ቢኖርም  የኤርትራ ልምድ ብዙ እንዳንል ያደርገናል፡፡ ስለዚህ  ጥሞና ያስፈልጋል!

በጥቂት ፖለቲከኞች ፍላጎት የተነሳ የየራሱን ትንንሽ መንግስት የመመስረት ዓላማ ያለው ክልልና ብሔር ተኮር ጠባብ አመራር ኢህአዴግን ወሮታል፡፡ ፓርላማው ህግ አያከብርም አያስከብርም፤ ስራ አስፈፃሚው ህግ አያከብርም አያስከብርም፤ የፍትህ አካሉ ተራ መጠቀሚያ  ነው፡፡ አሁን አገር ከማዳን ይልቅ፡ ቡድን ማዳን ቁልፍ ስራ የሆነበት አመራር የኢትዮጵያ ባለቤት ሆኗል፡፡  ቀንዳም  ከብቶች ጋጡን (በረቱን) እያመሱት ነው፡፡ ሁሉም ጭድና ገለባ ለእኛ ብቻ የሚሉ ቀንዳሞች የበላይነት ይዘዋል! ጂቲፒ 2 ምንድን ነው? በሉ ፤ ጅቲፒ 2 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው! ጅቲፒ 2 የሰላም ማስከበር ነው! ስለዚህ  ጥሞና ያስፈልጋል! የት ይደርሳል የተባለው…..

አገር የማዳን ሚና ያለው ጥሞና አስፈላጊ ሆኗል፡፡ የትኛው አካል ፤ መቼ መቼ ፤ ምን ዓይነት ውሳኔዎችን መወሰን ሲጀምር፤ለምን ነገሮች መበላሸት እንደጀመሩ መፍትሔ ለመስጠት በጥሞና ማሰብና በአስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ቀንዳም ከብቶች ባሉበት በረት መቀየር አልያም በረቱን ሰንጥቆ መለያየት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ቀንድ ለመቁረጥ አስቸጋሪ ሁኔታ መኖሩ ግልፅ ነው፡፡ መፍትሔው በረት የሚያምሱ ከብቶችን ሳይቀደሙ ወደቄራ መላክ ነው!! ሳይቀደሙ መቅደም !! በሬና ላሞች ከተመቱ ወይፈንና ጊደሮች ይበተናሉ! ያኔ አገር ይድናል፡፡ አሁን ፍፁም አስፈሪና አሳፋሪ ኢህአዴግነት እየታየ ነው፡፡ ኪራይ አዳኞች የበላይነታቸውን ተጠቅመው የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ነው! ስለዚህ የጥሞና መፍትሔ ያስፈልጋል!

Leave A Reply

Your email address will not be published.