በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የባሪያ ንግድ ሰለባ እንዳይሆኑ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው

(ኤፍ ቢ ሲ)- በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እየተፈፀመ ባለው የባሪያ ንግድ ሰለባ እንዳይሆኑ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚኖሩባቸው ቦታዎችም መለየታቸውን ገልጿል።

ዜጎቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በመግለጫቸው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ መንግስትም ካይሮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካኝነት ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ፥ መረጃ የማሰባሰብ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አቶ መለስ ጠቁመዋል።

በቀጣይም ለዜጎቹ የጉዞ ሰነድ የመስጠት እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።

አቶ መለስ ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ስኬታማ ለማድረግ ለሪፎርም የሚያስችሉ ስራዎችን እያካሄደ መሆኑንም ነው ያነሱት።

እየተካሄዱ ካሉት የሪፎርም ስራዎች ውስጥ አዲስ ድርጅታዊ መዋቅር የማጥናት ስራ፣ የሰው ሀብት ስምሪቱን ወጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ፣ የአቅም ግንባታ ማሻሻያ የሚሉት ይገኙበታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.