በመጪው ዕሁድ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባውን ይጀምራል

(EBC)- በመጪው ዕሁድ መጋቢት 2፣ 2010 ዓ.ም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባውን እንደሚጀምር የኢህአዴግ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

ስብሰባው እንደተጠናቀቀ የኢህአዴግ ምክር ቤት የግንባሩን ሊቀመንበር እንደሚመርጥ የግንባሩ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታውቀዋል፡፡

የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመረጠው ግለሰብ ጠ/ሚንስትር እንደሚሆን የምክር ቤቱ ህገ ደንብ ይደነግጋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.