በሞዛምቢክ በእስር ላይ የነበሩ 47 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ትናንት ምሽት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በህገ-ወጥ መንገድ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ በሞዛምቢክ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው።

ስደተኞቹ በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ጥረት ትናንት ምሽት ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ቀሪዎቹ ሰባት ስድተኞች ደግሞ ዛሬ ማምሻውን ይመለሳሉ።

መንግሥት በደቡብ አፍርካ የኢፌዴሪ ኤምባሲ በኩል ባደረገው ጥረት ለአገራቸው በመግባታቸው አመስግነዋል።

ስደተኞቹ የትራንስፖርት ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደየመጡበት አካባቢ አንዲመለሱ ተደርጓል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.