በተለምዶ ቆሼ በሚባለው አካባቢ የደረሰውን አደጋ መንስኤ የሚያጣራ ቡድን ተቋቋመ

በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ደርሷል፡፡ ከሟቾቹ 75 ሴቶች ሲሆኑ 38 ደግሞ ወንዶች ናቸው፡፡

በተያያዘ ዜና በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጐዱ ቤተሰቦች የምግብና የቁሰቁስ ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡

ግለሰቦች፣ ህብረተሰቡ፣ የሃይማኖት የተቋማትና ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የቆሻሻ መደርመስ መኖሪያ ቤታቸውን ያጡ በቦታው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በአካባቢው በተቋቋመው ጊዚያዊ ማቆያ መንደሮች ተጠልለዋል፡፡

ከአደጋው የተረፉ የሟች ቤተሰቦች በአከባቢው ባለ መኖሪያ ቤቶች በድንኳን ውስጥ በህብረት ተቀምጠዋል፡፡

በአደጋው ለተጎዱ ግለሰቦች በበቂ ሁኔታ ባይሆንም ከተለያዩ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ማህበራት እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

በበጎ አድራጎት ማህበራቱ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የግል ተቋማት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደርጉላቸው መሆኑን ታዝቧል፡፡

ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ተከፍቶ የእርዳታ ማሰባሰቢያው ስራ ቀጥሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአደጋው ለተጎዱና መጠለያ ላጡ ወገኖች የሚውል 200ሺ ብር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡

በቆሼ የቆሻሸ መደርመስ ለተጎዱ መጠለያ ላጡ ሰዎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ በተሸሻለ መልኩ መቀጠል እንዳለበት ተመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጎጂዎቹን በቋሚነት ለመቋቋም ጥረት እንደሚያደርግ ማስታወቁ ይታወሳል፡

 

ተቋማቱ በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ ለደረሰባቸው  ተጎጅዎች የ1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ ክምር መደርመስ   ባደረሰው አዳጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ ኢትዮ- ቴሌኮም የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን  ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክተቷል፡፡፡፡

ተቋሙ በቀጣይም ተጎጅዎችን በቋሚነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ድጋፉን ያደረገው ሁሉም አካላት በድጋፉ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ መሆኑን  ተቋሙ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ  የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን  ለተጎጂ በተሰቦች የ324 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የተጎጂ ቤተሰብ 4 ህፃናትንም ለማስተማር ቃል ገብተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤትና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እያንዳንዳቸው ለተጎጂዎች የሚውል የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.