በትግራይ ክልል የሰማዕታት ቀን እየታሰበ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- በሃውዜን የተጨፈጨፉ ሰመዓታት የሚታሰቡበት የሰመዓታት ቀን በትግራይ ክልል እየታሰበ ይገኛል።

የሰማዕታት ቀኑ በትግራይ ክልል የሚታሰበው ሰኔ 15 1980 በአየር ጥቃት የተሰው 2 ሺህ 500 ዜጎችን ለማሰብ ነው።

የመታሰቢያው ቀን በዛሬው ዕለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶ በትግራይ ክልል እየተሳበ ይገኛል።

በመቀሌ ከተማም እየተካሄደ ባለ ታላቅ ሰልፍ እለቱ እየታሰበ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም የሰማዓታት በዓልን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ንጹሃን ወገኖቻችን እልቂት እሩብ ምእተ አመትን መሻገሩ እውን ቢሆንም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ህመሙን እና ሀዘኑን የዛሬ ያህል እየታመመ ይግኛል ብለዋል።

የሀውዜን ጥቃት ለዛሬ ሀገራዊ አንድነት እና ኢትዮጵያዊ ህልውናችን የትናንት መሰረት መሆኑን አስታውቀዋል።

ሰማዕታትን ይበልጥ ከማክበር፣ ከመዘከር እና ታሪካቸውን ለመከተብ ሁሉም ዜጋ ሀላፊነት እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፥ መንግስትም ለሰማዕታት ተገቢውን ክብር ለመስጠት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.