በአዳማ ኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ በኤሌክትሪክ ምክንያት የእሳት አደጋ ደረሰበት

(ኤፍ.ቢ.ሲ):- አዳማ ከተማ የሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ቃጠሎ ደረሰበት።

በኤሌክትሪክ መስመር ምክንያት እንደተነሳ በተገለጸው የእሳት አደጋ ቃጠሎ የሆቴሉ አብዛኛው ክፍሎች መውደማቸው ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅትም የከተማው ነዋሪዎች፣ ፖሊስ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ኮማንድ ፖስቱ በመተባበር ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.