በደቡብ ምሥራቅ ዕዝ 18ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ የጀግንነት ሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተለት

ሻለቃው ሽልማቱ የተሰጠው የአገር አቀፍ የመከለከያ ሠራዊት ቀን በጅግጅጋ ሲከበር ነው፡፡

ለ5ኛ ጊዜ በተከበረው በዓል ላይ ሻለቃው ሜዳሊያውን የተሸለመው አልሸባብን በመዋጋት ረገድ ላሳየው ጀብዱ ነው፡፡ የሶማሊያው የሽብር ቡድን ባሳለፍነው ሰኔ 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ሠፈር የሰነዘረውን ጥቃት የክፍለ ጦሩ ሻለቃ በከፍተኛ ወታደራዊ ብቃት መልሶታል፡፡

ሽልማቱ በማንኛውም ዓውደ ውጊያ የጀግንነት ተግባር ለፈፀሙ የሠራዊቱ አባላት እንዲበረከት በአዋጅ የተፈቀደ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.