ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሮሞኛ ቋንቋን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

(አብመድ)- የዩኒቨርሲቲው የሂዩማንቲ ፋኩልቲ ዲን ዶክተር ዳዊት አሞኘ እንደተናገሩት የግዕዝ ቋንቋን ከጥንታዊቷ ኢትዩጵያ ታሪክ ጋር በማቀናጀት ማስተማር ለመጀመር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ከግዕዝ በተጨማሪ የኦሮምኛ ቋንቋን ለማስተማር የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና ሌሎች ጥናቶች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ፋኩልቲው ቲያትር እና ፊልም ለማስተማርም ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም ከፍቶ በአማርኛ ቋንቋ እድገት ላይ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.