ባለፉት ሁለት ወራት በምዕራብ ትግራይ በኩል ሰርገው ለመግባት የሞከሩ 98 የጸረ ሰላም ሃይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኤፍ ቢ ሲ)- ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በምዕራብ ትግራይ ዞን በኤርትራ በኩል የሽብር ተልዕኮ ይዘው ወደ መሃል ሃገር ለመግባት የሞከሩ 98 የጸረ ሰላም ሃይሎች ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የጸረ ሰላም ሃይሎቹ በኤርትራ ሃገር ከሚኖረው የግንቦት ሰባትና የኦነግ የሽብር ቡድን፥ የሽብር ተግባር ተልዕኮ ወስደው የገቡ ናቸው ተብሏል።

የዞኑ አስተዳደር ምክትል ዋና አዛዥና የጸጥታ ዘርፍ አስተዳደር ሃላፊ አቶ ተክዩ መተኮ፥ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በመከላከያ ሰራዊትና በዞኑ ነዋሪዎች በተደረገ ጠንካራ የክትትል ስራ የጸረ ሰላም ሃይሎቹ ሾልከው ወደ መሃል ሃገር ሳይገቡ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከእነዚህ 98 ጸረ ሰላም ሃይሎች ውስጥ 15ቱ በያዝነው ሳምንት ወደ መሃል ሃገር ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።

የሽብር ሃይሎቹ ወደ መሃል ሀገር በመግባት በአኮኖሚና ማህበራዊ ተቋማት ላይ አደጋ ለማድረስ ከሽብር ቡድኑ ተልዕኮ የተቀበሉ እንደነበሩም ተገልጿል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.