ባለፉት አራት ወራት 156 በኤርትራ የመሸጉ የሽብር ቡድን አባላት እጃቸውን በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

(ኤፍ ቢ ሲ) በኤርትራ ለሽብር ተግባር ተሸሸግው የነበሩ 156 የግንቦት 7፣ የኦነግ፣ የደምሒት እና የሌሎችም ፀረ ሰላም ቡድን አባላት እጃቸውን በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

የምእራብ ትግራይ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፀጥታ ዘርፍ አስተዳደር ሃላፊ አቶ ተኪኡ መተኮ እንደተናገሩት፥ የፀረ ሰላም ኃይል አባላቱ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ባለፉት አራት ወራት ነው።

አባላቱ በኤርትራ ከተሰማሩበት የሽብር ተግባር ራሳቸውን በማውጣት፥ በሀገሪቱ ውስጥ በሰላም ለመኖርና ለማልማት ፈልገን ነው የመጣነው ማለታቸውን ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት 160 የሚበልጡ የሽብር ቡድን አባላት፥ ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በሰላም እጃቸውን መስጠታቸው ይታወቃል።

ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ ሁለት 2009 ዓ.ም ባሉት ቀናት ብቻ የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ 48 ታጣቂዎች በቡድንና በተናጥል በመግባት ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.