አለም አቀፉ የስደተኞች ቀን የፊታችን ማክሰኞ በጋምቤላ ይከበራል

(ኤፍ ቢ ሲ)- አለም አቀፉ የስደተኞች ቀን የፊታችን ማክሰኞ በጋምቤላ ክልል ይከበራል።

ኢትዮጵያ የአለም ስደተኞች ቀንን እንድታስተናግድ መመረጧ እያበከተችው ላለው አስተዋጽኦ እውቅናን የሰጠ ነው ተብሏል።

ቀኑ “አጋርነት ለስደተኛ ወገኖቻችን” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ክልል ጉኝየል የደቡብ ሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ነው የሚከበረው።

ቀኑ በኢትዮጵያ እንዲከበር መደረጉ ለስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እና ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት ለማጉላት እንደሚረዳ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን በበዓሉ ላይ ይታደማሉ።

ኢትዮጵያ ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞች ተቀብላ በማስተናገድ በአፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ ትገኛለች።

Leave A Reply

Your email address will not be published.