አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)-n የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው ነው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የቀረበለትን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሰባት የቦርድ አባላትን ሹመት ያፀደቀው።

በዚህ መሰረት አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሾሙ፥ አቶ ደሞዜ ማሜ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ምክት ቤቱ በተጨማሪም የሰባት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል።

አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ከ1972 እስክ 1998 በኢትዮጵያ ማእከላዊ ስታስትቲክስ ኤጀንሲ ውስጥ ከቡድን መሪነት አንስቶ እስከ ምክትል ስራ አስኪያጅነት ሰርተዋል።

ከ1998 እስከ 2009 ዓ.ም ደግሞ የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲን በዋና ዳይሬክተርነት መርተዋል።

አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.