‘አንፀባርቀሻል/ሃል/’

(አባዲ ከሾላ) – ወትሮ በትጥቅ ትግል ወቅት የነበረ የግምገማ ሁኔታ ነው፡፡ እያሱ በርኸ በሸገር ሬዲዮ ከመዓዛ ብሩ ጋር ቃለመጠይቅ ሲያደርጉ እንዳወጋት ፡፡ ቀደም ሲል በትግራይ እና አካባቢው የነበሩ ሽፍቶች ሴትን መድፈር እና ማሰቃየት፡ መዝረፍ ዋነኛ መገለጫቸው በነበረበት ወቅት ህወሓትና ኢህዴን ያንን ህዝብ ያማረረ ተግባር ለመቃወም እና በሌሎችም ምክንያቶች ፆታዊ ግንኙነትን በትግል ወቅት ለአስር አመታት ከልክለው ነበር ይባላል፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ በዚህ ተግባር የተገኘ ታጋይ ከፍተኛ ቅጣት ይጣልበት ነበር፡፡ በተለይ ሴት ታጋዮች ወንድ ታጋዮችን ወደ ‘ፆታዊ አምሮት’ የሚገፋፋ ተግባር የፈፀሙ እንደሁ በዋናነት ተገምጋሚዎች ነበሩና ‘አንፀባርቀሻል’ ይባላሉ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤ በየትኛውም ተልዕኮ ውስጥ ከወንዶች ጋር የተሰለፈች ታጋይ ሰውነቷን የሚያጋልጥ አለባበስ ክልክል ነው፡፡ ሰውነቷን ካሳየች ፤ አብዛኛው ታጋይ በበረሃ ትቢያ ውስጥ ሲማስን ድንገት በጊዜው በነበሩ ሳሙናዎች ተጣጥባ ፀድታ የታየች እንደሆን ‘አንፀባርቀሻል’ ትባላለች፡፡ በየትኛውም መልኩ የማማለል ሙከራ፡ ማንፀባረቅነው፡፡

#ዘንድሮ በኑሮ ደረጃቸው ህዝብ ላይ የሚያንፀባርቁ አመራሮችን እንደልብ በምናይበት ዘመን ‘አንፀባርቀሃል’ የሚላቸው ቢኖር አልኩ፡፡

  • አመራር በአኗኗሩ ህዝቡን ሲያማልል አላንፀባረቀም?
  • ህዝብ በድህነት ትቢያ ውስጥ ሲማስን በዝርፊያ ውስጥ ያለ ሁሉ አላንፀባረቀም?
  • የራሱን ቪላ ገንብቶ በማከራየት መንግስት የሚሰጠውን መኖሪያ የሚያማርጥ፡ ህዝብ ላይ አላንፀባረቀም?
  • አምና በከፈለቻቸው አገር ‘የክፉ ቀን ማምለጫ’ በሚል የሀገር ሀብት በውጭ አገር የሚያከማች ባለሃብትና ባለስልጣን አላንፀባረቀም? እረ ስንቱ…

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.