አውሮፓ ሕብረት በድርቅ ለተጎዱ ሃገራት 165 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠ

 

አውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያና ለሌሎች በቀጣናው በድርቅ ለተጎዱ ሃገራት 165 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠ፡፡ከኢትዮጵያ በዘለለ ሶማሊያ፣ኬኒያና ደቡብ ሱዳን ከድጋፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ይህ ይፋ የሆነው፣የአውሮፓ ሕብረት የውጭና የጸጥታ ጉዳይ ተወካይና የህብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍሬድሪካ ሞግኸርኒ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ሞግኸርኒ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ፣በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ሕብረታቸው የሚኖረውን ሚና በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ መንግስት ከተቃዋሚዎቹ ጋር የሚያደርገውን ድርድርም የአውሮፓ ሕብረት እንዲሚያደንቀው ሞግኸርኒ ለአቶ ኃይለማርያም ነግረዋቸዋል፡፡በድርድሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እንዲኖርም ጠይቀዋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት የሚመጡ ስደተኞችን በመቀበል የምታደርገውን ትብብር ለማገዝ የአውሮፓ ሕብረት ድጋፉን እንደሚቀጥል ሕብረቱ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኪኖሚያዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ ሕብረቱ የሚያደርገው ድጋፍም ቀጣይነት ያለው ነው ተብሏል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.