አዲስ አበባና የፈረንሳይዋ ግራንድ ሊዮን ከተማ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢዜአ)- አዲስ አበባና የፈረንሳይዋ ግራንድ ሊዮን በከተማ ልማት ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረበትን 20ኛ ዓመት አስመልክቶ “ዘላቂ የከተሞች ግንባታ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ” በሚል መሪ ሃሳብ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመዲናዋ ተወያይቷል።

ከኢትዮጵያ ልማት ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ውይይት አዲስ አበባና የፈረንሳይዋ ግራንድ ሊዮን በከተማ ልማት ስራዎች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው፣ የሊዮን ከተማ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚስተር ፓትሪስ ዴብዤ እና በፈረንሳይ የልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢኛስ ሞንካም ዳቬራ ናቸው።

የከተሞች እድገትን ለማስቀጠል ምን መሰራት ይኖርበታል

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደምሴ ሽቶ ባደረጉት ንግግር “የዕድገታችን ሞተር የሆኑት ከተሞቻችን ዕድገት ዘላቂ እንዲሆን የመሰረተ ልማት ዕጥረት፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አቅም ውስንነት፣ የስራ እድልና የቆሻሻ አወጋገድ ችግሮችን መፍታት አለብን” ብለዋል።

በአገሪቷ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ የሥራ መስኮች ከሚያስፈልገው የሰው ሃይል ከተሞች 15 በመቶውን በማቅረብ ለዓመታዊ እድገቱ የ38 በመቶ ድርሻ በማበርከት ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ ትልቅ አቅም እንደነበሩም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የከተሞች እድገት በየዓመቱ ከአምስት በመቶ በላይ እንደሆነ ገልፀው በዚሁ ከቀጠለ ከ30 ዓመታት በኋላ ከአገሪቷ ህዝብ 40 በመቶው ወይንም 54 ሚሊዮን ያህሉ በከተማ እንደሚኖር የሚያሳይ ትንበያ መኖሩን ነው የተናገሩት።

እንደ አቶ ደምሴ ገለጻ ከተሞች በፍጥነት እያደጉ ቢሆንም የከተሞች ፕላን፣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት፣ የፍሳሽና ቆሻሻ አያያዝ፣ የሰዎች ፍልሰትና ሌሎች ፍላጎቶች በሚገባ እየተፈቱ ካልሄዱ የከተሞቹ እድገት ወደ ኋላ ሊመለስ ይችላል።

ለዚህ ደግሞ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሰረት የተቋማትን የመፈጸም አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የስራ እድል ፈጠራ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ልማትና ሌሎች ተግባራትን በሚገባ መከወን ያስፈልጋል።

በኢትዮጵያ የከተሞች የስራ አጥ መጠን 15 በመቶ መድረሱን የተናገሩት አቶ ደምሴ አሁን ባላቸው እድገት መሰረት በመጪዎቹ 15 ዓመታት ስድስት ሚሊዮን የስራ ዕድሎችን መፍጠር ያስፈልጋል፤ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትም በአምስት ሚሊዮን ይጨምራል ብለዋል።

የፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ፍሬድሪክ ቦንተምስ በበኩላቸው መንግስታቸው በኢትዮጵያ የከተሞችና የሃይል ልማት እንዲሁም ለግል ባለሃብቶች ድጋፍ በሚደረገበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት አድርጎ አየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት የከተሞችን መሰረታዊ ፍላጎቶች ከመመለስ አንጻር በተለይም በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በሃይል ልማት፣ በከተሞች የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በቆሻሻ አወጋገድና በከተሞች ፕላን ልዩ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሰዋል።

አምባሳደሩ እንደሚሉት በድርጅቱ የኢትዮጵያ የሃያ ዓመታት ቆይታ ለሃምሳ የልማት ፕሮጀክቶች የ522 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ 455 ሺህ ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኙ፣ የተሳለጠ የከተማ ትራንስፖርት አስተዳደርና ሌሎች ስራዎች ድጋፍ ተደርጓል።

አገልግሎት በመስጠት ላይ ላለው አሸጎዳ የንፋስ ሃይል ማመንጫ፣ ለቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያ፣ በአፋር ክልል በመልማት ላይ ለሚገኘው የከርሰ ምድር ሃይል ማመንጫ፣ ለአየር መንገድ ሙያተኞች ማሰልጠኛ፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ላኪዎችም ድጋፍ ሰጥቷል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ከተሞች አስተዳዳሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን በከተሞች መስፋትና ፈተናዎች ዙሪያ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

2 Comments
 1. ethoash says

  distributing technology … what we need is not asphalt road but concrete road
  here is the reason

  Roller-compacted concrete (RCC) is an ultra-tough, zero-slump concrete with
  compressive strengths greater than 4,000 psi. It is placed with asphalt pavers to form
  a nonreinforced, concrete pavement. RCC successfully and economically combines
  strength and durability with ease of construction.

  RCC consists of portland cement, coarse and fi ne aggregates, and water.
  RCC requires no forms, fi nishing, steel reinforcement or joint sawing. However,
  saw-cut joints can be easily created to offer an enhanced appearance and to
  help control cracking.

  Can also be used for surfaces and rehabilitation of:
  • Streets and local roads
  • Residential streets
  • High-volume intersections/roads (rehab)
  • Airport aprons and taxiways
  Solutions Provided:
  • Low initial cost – RCC is competitive with alternative pavement options
  on a fi rst-cost basis.
  • High durability – Resists rutting and will not deform under heavy,
  concentrated loads.
  – Resists deterioration from fuel and hydraulic fl uid spills
  – Performs well in freeze-thaw climates
  – Supports heavy, repetitive loads without failure and spans localized,
  soft subgrade areas
  • Low maintenance – Fewer associated costs
  – No need for surface sealing or overlays
  • Reduces down time – Fast return to service and minimizes elevation
  changes for rehab projects
  Features:
  • Fast construction – With no forms or fi nishing and minimal labor,
  RCC is placed quickly
  – The low water-to-cement ratio and zero slumb consistency of the mix
  allows for quick strength gain.
  • Quick return to service – RCC pavement can often be opened to local
  traffi c in as little as 4 hours after placement and can accept heavy traffi c
  24-48 hours after placement.
  • Lighter surfaces – Reduce urban heat island effect and lighting
  requirement for parking and storage areas.
  • Strong – High fl exural strength (500 to 1000 psi)
  – High compressive strength (4,000 to 10,000 psi)
  – High shear strength
  – Low shrinkage
  • Simple design/Construction – No steel reinforcing or dowels
  – Aggregate interlock provides excellent load transfer, eliminating need
  for dowels.
  – No forms or fi nishing
  – Joint sawing is optional for aesthetic purposes

 2. ethoash says

  Uploaded on May 16, 2011
  Roller Compacted Concrete (RCC) is the optimal pavement construction solution for local streets and roads. In this video, hear how RCC’s installation and maintenance costs are lower than asphalt, as it provides for a more durable pavement solution. RCC is ideal for the urban environment as it allows for roads to be quickly reopened for traffic in as little as one day.

  This video explains how RCC got its start in the seventies and how its use has evolved through the years to other applications such as dams, parking areas, distribution areas, highway shoulders, industrial pavements, and now — with innovations in mix designs, new equipment and grinding technology — local streets and roads.

  Andy Johnson of the South Carolina Department of Transportation explains the success his state has had with RCC on road construction projects since 2003. To date, he has worked on numerous projects with very favorable, cost-effective results. He exemplifies this by describing how in one specific project, it took only 15 days to complete a one-mile long, 4-lane wide rehabilitation which required milling 10 inches of the existing surface and replacing it with RCC. It would have taken 33 days to complete had asphalt been used. In other words, using asphalt would have doubled the construction time, further impacting access to local businesses.

  In terms of construction costs, RCC is typically equal to or as much as 20% lower than asphalt, depending on the project. Additionally, the life cycle costs of RCC when compared to asphalt are about 30% lower.

  The basic ingredients of RCC are the same as for conventional concrete: sand, aggregates, cement, and water. Mix designs may vary based on the job application. Mixing is usually done on or near the work site, and is delivered in dump trucks. RCC is placed much drier than conventional concrete, which results in higher compressive and flexural strengths. It is placed with asphalt pavers, and then compacted with rollers. It needs no forms or reinforcing steel. Placement is straightforward: mix it, place it, compact it, and cure it.

  Not only is RCC the optimum choice for pavements, but it also supports sustainable development. RCC pavements provide high solar reflectivity, which helps mitigate the urban heat island effect

  RCC is used in NIle dam

  here is the video

  https://www.youtube.com/watch?v=CP8zjaT35X8

Leave A Reply

Your email address will not be published.