ኢትዮጵያስ እንጃላት

(ኡስማን ከለገጣፎ ) – በዚህ ሳምንት አምቦ ላይ ዶ/ር መራራ ጉዲናን ለመቀበል የወጣ የህዝብ ማዕበል አየሁ። በሰላማዊነቱ ደስም አለኝ። ነገር ግን ከእዛ የህዝብ ማዕበል መሀከል አንዲትም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳልተወለበለበ ስመለከት እንደሀገር መለያየታችንን አወቅኩ። አንድ እንኩዋን የፌደራል መንግስቱ ሰንደቅአላማ ይጥፋ? ባንዲራው ባለኮከቡ ወይንም ልሙጡ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እንደው አንድ እንኩዋን የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማ የሚይዝ ይጥፋ???

አይ ሀገሬ፤ አሁንስ ፈራሁልሽ። የጋራ የምንለው ነገር ተበጣጥሶ እየጠፋ ነው። የሚገርመው ደግሞ የአንድነት ሃይሎች የሚባሉት ሳይቀር በማህበራዊ ሚድያ ፎቶውን በድል ሲቀባበሉት ማየታችን ነው። እንደ ሊብያ የትሪፖሊ እና የቤንጋዚ ባንዲራ አይነት መኮኑ ነው?

እንጃ ብቻ፤ ኢትዮጵያስ እንጃላት!

ኡስማን ከለገጣፎ

Leave A Reply

Your email address will not be published.