ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራ ከ54 ሺህ በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች

(EBC)- ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በአብዛኛው ከኤርትራ፤ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን አገራት የተሰደዱ ከ54 ሺህ በላይ ስደተኞችን መቀበሏን ተገልጸ፡፡

የስደተኞችና ከስደተ ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር እንደገለጸው ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 850 ሺህ ስደተኞችን ከኤርትራ፤ ሱማሊያ፤ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን አገራት የመጡ ስደተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
የአስተዳደሩ ምክትል ደይሬክተር አቶ ዘይኑ ጀማል እንዳብራሩት በአለም አቀፍ ደረጃ ከ65 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያም ስደተኞችን በማስተናገድ ከሚጠቀሱ አምስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆናለች፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.