ኢትዮጵያ ከውሃ የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች

(EBC)- ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ኃይል በማመንጫት ቀዳሚ መሆኗን አለም አቀፉ የውሀ ኃይል ማመንጫ ማህበር አስታወቀ።

ማህበሩ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በውሃ 3,822 ሜጋዋት በማመንጨት ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም አንጎላን በማስከተል ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች። ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ማህበሩ 6 ሺህ 450 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይ መሆኗንም ገልጿል።

በአራት ቢሊዮን ዶላር አንድ ሺህ ሜጋ ዋት የሚያመነጩ ሁለት የከርሰ ምድር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሷንም ጆርናል ካሜሮን ድረ-ገጽ  ዘገባው አመልክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.