ኢትዮጵያ የቡድን 77 እና ቻይና ሊቀመንበር ሆነች

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- ኢትዮጵያ የ2018 የቡድን 77 እና ቻይና (የናይሮቢ ቻፕተር) ሊቀመንበርነት ቦታ ከፓኪስታን ተረክባለች። ሊቀመንበርነቱን የተረከቡት በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው።

ቡድኑ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ለታደጊ አገሮች ድምጽ መሰማት የሚያደርገው ጥረት የሚደንቅ መሆኑን የተጠቀሱት አምባሳደር ዲና በእርሳቸው የሊቀመንበርነት ዘመንም ቡድኑ በተባበሩት መንግስታት ስርዓት ውስጥ የታዳጊ አገሮች ጥቅም ለማስጠበቅ እና ድምፃቸውን በጋራ ለማሰማት የሚደርገው ሚና ተጠንክሮ እንሚቀጥል ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ቀጣይነት ያለው ልማት ዋነኛ ምሰሶዎች የሆኑትን በቀጣይነት ተጠናክረው መፈፀም እንዳለባቸው እና ኢትዮጵያ ለዚህ ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም ሊቀመንበር እንደመሆኗ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም በአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ አገራት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በጋራ እንደምትሰራ እና ድርሻዋን እንደምትወጣ አምባሳደር ዲና ገልፀዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.