ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት የንግድና ኢንቨስትመንት አውደ ርዕይ በኩዌት ተካሄደ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- ኢትዮጵያን ጨምሮ የ25 የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች የተሳተፉበት የንግድና ኢንቨስትመንት አውደ ርዕይ በኩዌት ተካሂዷል።

አውደ ርዕዩን ያዘጋጀው የኩዌት ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ነው።

ኤምባሲዎቸየ የየራሳቸውን የማያ ቦታ በመውሰድ የየአገሮቻቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን አሳይተዋል።

ሚሲዮናችንም የማሳያ ቦታ በመያዝ የአገራችንን ምቹ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የቱሪዝም እድሎችን አስተዋውቋል።

የኩዌት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ካሊድ አልጃራላህ እና የኩዌት ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ምክትል የቦርድ ሊቀ-መንበር አብዱልዋሃብ አልዋዛን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በኩዌት የኢፌዲሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አብዱላዚዝ አህመድ በቦታው በመገኘት አገራችንን የሚያስተዋውቁ ስጦታዎች ለክብር እንግዶቹ ከማበርከት በተጨማሪ ስለሀገራችን መግለጫ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት፣ የንግድና ቱሪዝም አማራጮችን የሚያሳዩ የተለያዩ የማስተዋወቂያ ሰነዶችንና የቡና ናሙናዎች ለኤግዚቢሽኑ ጎብኝዎች ተሰራጭተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.