ከ ENN Tv የተሰጠ መግለጫ

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የብሮድካስት ባለሥልጣን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ከኢ.ኤን.ኤን ቴሌቪዥን የተሰጠ ምላሽ

.ኤን.ኤን ቴሌቪዥን ስርጭቱን ከጀመረበት ጊዜ12/7/2008 . ጀምሮ በዜና፣ በወቅታዊ እና በትንታኔ ሰጪ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዋነኛ ትኩረቱን በማድረግ ስፖርት እና መዝናኛ በማካተት ለህብረተሰብ መረጃ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተለይ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በትኩስ መረጃዎች ላይልዩ ትኩረት በማድረግ በየሰዐቱ ዜናዎችንከማቅረቡም በላይ በሀገራችን ላይ በሚከሰቱ ሀገራዊ ሆነ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በተለይ በህገመንግስታችን ላይ በሰፈረው ሀሳብን የመግለፅ ነጻነት መሰረት በማድረግ ልዩ ልዩ አመለካከት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳባቸውን በነፃነት የሚያንሸራሹሩባቸው ፕሮግራሞች በመቅረፅ የሀሳብ ነፃነትን ምህዳር በማስፋት ረገድ የግንባር ቀደምትነት ሚና በመጫወት በርካታ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ እንደቆየ ይታወቃል፡፡

በዚህም አብዛኞቹ የሃገራችን ሚዲያዎች ትኩረታቸውን ወደ ስፖርት እና መዝናኛ መስክ በስፋት ሰጥተው በሚሰሩበት ወቅት ላይ . ኤን. ኤንቴሌቪዥን በየሰዓቱ በሚያቀርባቸው ዜናዎች በተለይም የህዝብ ቅሬታ ዜናዎች ላይ በማተኮር መስራቱ ሳምንታዊ የፊት ለፊት ቃለ መጠይቅ፣ ሳምንታዊ ኦዳ ነጻ ሀሳብ መድረክ፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ ደግሞ ዳጉ የህትመት ዳሰሳ በቀጥታ ከህዝብ ጋር የሚያገናኘው ህዝብ ድምፅ በሴቶችእና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ጣይቱ፣ በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ትኩረት የሚያደርገው ዮጵ የተሰ ታለንት ሾው፣ እንዲሁም በየዕለቱ የሚቀርበው የልጆች ተራ የተሰኘው የህጻናት ፕሮግራ በምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውቀይ ባህር እና ሌሎች በርካታ መሠል ፕሮግራሞችን በነፃነት ማቅረብ አጭር ጊዜ ታዋቂነት እና ተቀባይነት ማግኘት መቻሉ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በገዢውም ሆነ በተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሰጡ ማናቸውም መግለጫዎች ያለአንዳች ገደብ እና አድልዎ ከማስተናገዱም ባሻገር በልዩ ልዩ መድረኮች ላይ የሚንሸራሸሩ ሀሳቦችን ሳይቆራረጡ እንዲተላለፉ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን ካሁን ቀደም ሲደረግበት የነበረው ጫና እና የመነጠል ስራ ተቋቁሞ ስራውን ሲያከናውን ባለበት በዚህ ወቅት ደግሞ መብቴን ያስከብርልኛል ከሚለው ተቋም ሌላ ደንቃራ ተከስቶበታል፡፡

ይኸውም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የብሮድካስት ባለስልጣን በቁጥር .. /2092/3147 19/10/ 2010 ለኢ.ኤን.ኤን. ቴሌቪዥን በፃፈው ደብዳቤ ‹‹በሰኔ 16 የተካሄደውን የእውቅና እና የድጋፍ ሰልፍ . ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን በእለቱ የስርጭት ሽፋን አልሰጠውም፡፡ በመሆኑም ለሰላማዊ ሰልፉ የስርጭት ሽፋን ያልሰጣችሁበትን ምክኒያት ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ›› በሚል ተጠይቀናል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ‹‹ህገወጥ ስርጭትን በሚመለከት ቁጥጥር ማድረግ›› በሚል ከተሰጠው ሀላፊነት ውጪ ይህንን ዘግብ ያንን አትዘግብ ሚል የኤዲቶሪያል ጣልቃ ገብነት ይህን መሰል ጥያቄ ማቅረቡ በአጠቃላይ በሚዲያ ስራ ላይ ተሰማሩ ባለሙያዎች አሳፋሪ ትዕዛዝ ሲሆን ለኢ. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን ደግሞ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን አስፈሪ መልዕክት ያዘለ አቅጣጫ ጠቋሚ ትዐዛዝ እንደሆነም መግለፅ እንወዳለን፡፡

በዚህም መሰረት የኢ. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን ኤዲቶሪያል የስርጭት ሽፋን የሰጠበትን ምክኒያት እና የቀረበበትን መሰረተ ቢስ ውንጀላ በማስመልከት ምላሹን እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን በሰኔ 16 የተካሄደው ዝግጅት ላይ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፉን ለመዘገብ ብሎም በቀጥታ ለማስተላለፍ ከአዘጋጅ ኮሚቴው በደብዳቤም ሆነ በስልክ ምንም አይነት ጥሪ ያልቀረበልን መሆኑ እየታወቀ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴውም ስለመዘገባችን ወይም ስለአለመዘገባችን፣ ጥሪ ስለማድረጉም ሆነ ስለአለማድረጉ ምንም አይነት መግለጫ ባለሰጠበት ሁኔታ ሰልፉን በማዘጋጀትም ሆነ ሚዲያዎችን በማስተባበር ምንም አይነት ሚና ያልነበረው አካል ጣልቃ ገብቶ ቁጣውን መግለጹ አስገርሞናል፡፡

. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን ምንም እንኳን ከአዘጋጁ አካል ጥሪ ባይቀርብለትም ይህንን ህዝባዊ ሁነት መዘገብ አስፈላጊ እና ተገቢም ነው ብሎ በማመን ጋዜጠኞችን እና የካሜራ ባለሙያዎችን በመላክ አስፈላጊውን ቀረጻ ከማከናወኑም በላይ በዕለቱ ዜና ዘገባችን ዘጠኝ ያህል የድጋፍ ሰልፉን እና የደረሰውን አደጋ የተመለከቱ ዜናዎችን ሰርተናል፡፡ በተጨማሪም በክልል ከተሞች የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎችን ሽፋን ሰጥተናል፡፡ በማግስቱም 17/10/10 በቀንም ሆነበምሽት የዜና ዘገባችን በድጋፍ ሰልፉና በደረሰውአደጋ ላይ ሰፊ ሽፋን ሰጥተናል፡፡ የሰራናቸውንም ዜናዎች በኢ. ኤን. ኤን. የዩቲዩብ አድራሻ በመግባት ማግኘት እንደሚቻል ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ይህም ሊያስመሰግነን ሲገባ የሚያስወቅስ ሆኖ ይህን መሰል ደብዳቤ ድርጅታችን ላይ መጻፉ ጉዳዩ ‹‹ሳታመሀኝ ብላኝ›› እንድንል አስገድዶናል፡፡

በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጪ ያሉ ሚዲያዎች፣ ዌብ ሳይቶች እና የህትመት ውጤቶች በነጻነት እንዲሰሩ በይፋ ጥሪ በተላለፈበት በዚህ ወቅት በተቃራኒው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ /ቤት ጀምሮ ከማናቸውም ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ መግለጫዎች፣ ጉብኝቶች እና ህዝባዊ ሁነቶች እንዳንሳተፍ በተደረገበት በዚህ ሰዐት ይታደገናል ብለን የምናስበው የብሮድካስት ባለስልጣን መስሪያ ቤት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከሁሉ ከሁሉ ደግሞ በጣቢያችን ተቀጥረው በመስራት ላይ የሚገኙ በርካታ ወጣት ጋዜጠኞች፣ የፕሮግራም አቅራቢዎች እና ተባባሪ ፕሮዲውሰሮች ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ ሲያቀርቧቸው እንደነበሩት ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ፕሮግራሞችን ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በተነቃቁበት በዚህ ወቅት ላይ ይህን መሰል መግለጫ መውጣቱ የኢ. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ላይ የተካሄደ ሀሳብን የመግለጽ እመቃ እና ከህዝብ እና ከተቋማት የመነጠል ተግባር አጥብቀን የምንኮንነው መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመጨረሻም በእለቱ እና በማግስቱ ያለማቋረጥ በቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ ‹‹. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥንትናንት በተደረገው የምስጋና ሰልፍ ላይ የደረሰውንየቦንብ አደጋ እያወገዘ በደረሰው ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ በጥቃቱ ህይወቱን ላጣው ግለሰብ ወዳጆች እና ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡ ENN TV›› በማለት እንደገለጽነው አሁንም ቢሆን የደረሰውን ጥቃት የምናወግዝ እና ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ሀዘናችንን እየገለጽን ብሮድካስት ባለስልጣን የወጣውን መግለጫ በመቃወም ከኢ. ኤን. ኤን. ቴሌቪዥን እና ሀሳብን ከመግለጽ መብት ጋር አጋርነታችሁን ላሳያችሁን በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ የምትገኙ የሚዲያ ተቋማት፣ ታዋቂ አክቲቪስቶች የማህበራዊ ሚዲያ ፀሐፊዎች እና ድጋፍ ላሳያችሁን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

Leave A Reply

Your email address will not be published.