ካነበብኩት: “ባለ መንታ መንገድ የኮምዩኒኬሽን ስራ”

(ሸጊት ከድሬ) – “ህዝብን በልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ዙሪያ በማረባረብ ዉጤት ለማምጣት ግልፅነት በመፈጠር አሳምኖ ለማንቀሳቀስ ተግተን መስራት እንደሚየስፈልግ ሁሉ በኮሚዩኒካሽን ስራ ከአመራር ወደ ህዝብ ሃሳብ በማስተላለፍ ብቻ ሳይወሰኑ ህዝቡንም ስለስራዉ ምንነት፣ ስለነደፍናቸዉ ግቦችና ልዩ ልዩ ተግባራት አፈፃፀምና የእያንዳንዱ አባል ሚና አስተያየት እንዲሰጥ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኮመዩኒኬሽን ስራችን ሃሳቦች ከአመራር ወደ ህዝብ የሚንቆረቆሩበት እነደነበሩ ይታወቃል፡፡ ይህም መሆኑ አንዳችን ነጋሪ ሌላዉ አድማጭ እና ንቁ ያሆነ ተሳታፊ የሚሆንብት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ስራዎች በሚፈለገዉ ጥራትና የዉጤታማነት ደረጃ ሳይከናወኑ የሚቀሩበት ጊዜ ትንሽ አልነበረም፡፡ ይህን ይመሰለዉ ሂድት ተቀይሮ ዉጤታማና ጥራት ያለዉ ስራ መስራት ካለብን ከአንድ ወገን መልዕክት የማስተላለፍ አካሄደን ከሁለት አቅጣጫ የሃሳብ ልዉዉጥን በሚያበረታታ የኮምኒኬሽን ስርዓት ልንተካዉ መቻል አለብን፡፡

የኮምዩኒኬሽን ስራችን ባለ መንታ መንገድ አፈፃፀም ሊኖረዉ ይገባል ሲባል ህዝቡ በምናቀርብለት ሃሳብ ወይም እቅድ ዙሪያ ከአፈፃፀም አኳያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመጠቆም ብቻ ሳይወሰን የመፍትሔ ሃቦች በማምጣትም ከፍተኛ ሚና ስለሚጫወት ጭምር ነዉ፡፡ የምናቀርብለት እቅዶች በህዝብ ተሳትፎ የሚፈፀሙ መሆናቸዉና ህዝቡ ደግሞ ልዩ ልዩ ማበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና አስተዳደራዊ ችግሮች የሚያጋጥሙት በመሆኑ እነዚህን ሳናዉቅና ሳንፈታ በሙሉ አቅሙ ወደ እቅዱ አፈጻጸም ልንመራዉ አንችልም፡፡ በመሆኑም በማንኛዉም የዕቅድ ሃሳብ ዙሪያ ለማብራራትና ጠቀሜታዉን ለማስረዳት ብቻ ሳይሆን ሀዝቡ በዕቅዱ ይዘትም ሆነ በአፈፃፀም አቅጣጫዉ ላይ ችግር የሚለዉን ነገር እንዲያቀርብ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል ፡፡ ይህ ሲሆን ህዝቡ የሚያነሳቸዉን ችግሮች ፈትቶ በሙሉ መተማመን ወደ ተግባር ሊገባ ይችላል፡፡

ህዝቡ በእያንዳንዱ እቅድ ይዘትና አፈፃፀም ላይ አስተያቱንት እንዲያቀርብ በቂ እድል ማግኝት ያለበት ግን ችግሮች ለማንሳት ባለዉ ጠቀሜታ ብቻ አይደለም፡፡ ልማታዊ ተጠቃሚነቱ እየሰፋ፣ በመብቶቹም የመጠቀም ችሎታዉ እየዳበረ በሄደ ቁጥር ልምዶቹ እየዳበሩ፣ የአስተሳሰብ አድማሱና የፈጠራ ቸሎታዉ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነዉ፡፡ በመሆኑም የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግም ሆነ አጠቃላዩን የለዉጥ ጉዞ ለማጎልበት በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችን ማፍለቅ የሚችል ሆኗል፡፡ ባለመንታ መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ስራ መስራት ያለብን ከዚህ ጠቀሜ በመነሳትም ጭምር ነዉ፡፡

ይህን የመሰለዉን የኮሚዩኒኬሽን አቅጣጫ በተግባር ላይ እንዲዉል ለማድረግ በእያንዳንዱ እቅዳችን ላይ አጭር ወይም መለስተኛ ስልጠና መስጠት፣ ስልጠናዉ በበቂ ዝግጅት ላይ የተመሰረተ እንዲሆንና ለህዝቡም በየርዕሰ ጉዳዩ ሃሳብ እንዲሰጥ ሰፊ እድል የሚሰጥ ሆኖ ሊካሄድ ይገባዋል፡፡ በችግሩ ላይ ተወያይቶ ለመግባባት በሚደረግ ጥረት ህዝብን አስተያየቱን በዚሁ ላይ አተኩሮ እንዲሰጥ ማድረግ ከቻልን ልንፈታው የምንፈልገው ችግር እፋትና ጥልቀት እንዲሁም መግለጫ መልኮቹን ከህዝቡ አስተያየት በመነሳት እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ በመፍትሔ ሃሳቦችም ላይ በምንወያይበት ጊዜ ህዝቡ የሚታየዉን ሃሳብ እዲያቀርብ ማድረግ ችግሩን ከስረ መሰረቱ በመገንዘብ ሳንወሰን በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ችግሮቹን ለመቅረፍም ያስችለናል፡፡ በመሆኑም ከህዝብ ጋር ለመግባባት የሚደረግ ማናቸዉም ሙከራ ህዝቡን ከአድማጭነት ወደ ንቁ ተዋናይነት በሚቀይር አግባብ እንዲፈፀም ማድረግ ያስፈልገናል፡፡

  1. በመልዕክቶች አማካኝነት መግባባት መፍጠር፣

የህዝብ ግንኙነት ስራ በብዙ መንገዶች ሊከናወን የሚችልና የሚገባዉ የአስተሳሰብ መገንቢያ ስራ ነዉ፡፡ በትምህርት ቤቶች ዉስጥ ለአመታት የሚካሄድ የአስተምሮ ስራ ፣ የአጫጭርና መለስተኛ ስልጠናዎች፣ ሴሚናሮችና በአጫጭር መልዕክቶች አማካኝነት የሚካሄዱ የህዝብ ግንኙነት ስራዎቸደ ከብዙ በጥቂቱ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ህብረተሰብን ከመለወጥ አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ የህዝብ ግንኙነት ስራ ማስፈፀሚያ መሳሪያ በመልዕክቶች አማካኝነት የሚካሔድ ነዉ፡፡

በትምህርት ቤቶችና በሰፋፊ ስልጠናዎች አማካኝነት የሚካሔደዉ የህዝብ ግንኙነት ስራ እንደ አስፈላጊነቱ ለህብረተሰቡ በመላ ወይም ትርጉም ባለዉ ስፋት ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ብዙሃኑንና በዕለት ተዕለተ የምርት ተግባር የተጠመደዉን ህዝብ ረጅም ጊዜ ወስዶ በሚካሔድ የህዝብ ግንኙነት ስራ መለወጥ አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም፡፡ ህዝቡ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት በምርት ተግባር ላይ መጠመዱ አይቀርም፡፡ ይህም ለዉይይት የሚሆነዉን ጊዜ በእጅጉ ይቀንስበታል፡፡ ስለሆነም ህዝብን በማሳመን ለማንቀሳቀስ የሚፈለግ ማንኛዉም ሃይል በመልዕክቶች አማካኝነት ሊሰራ ይገደዳል፡፡

መልዕክቶች ከዚህ አኳያ ምን ማለት እንደሆኑ በጠራ አኳኋን በመገንዘብ ስራዉን በትክክል ለማከናወን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነዉ፡፡ በመልዕክቶች መስራት ሲባል የህብረተሰቡን ችግሮች ወይም የሚያነገበግቡትን ጉዳዮች ለይቶ በማዉጣት የእነዚህን መንስኤና መፍትሔ አስተሳስረዉ በሚያቀርቡ አጫጭር ሃሳቦች አማካኝነት መስራት ማለት ነዉ፡፡ ስለዚህም አንድን ህብረተሰብ በከፍተኛ ደረጃ ተፅዕኖ ሊያሳርፍበት የሚቸሉ አጫጭር ሃሳቦችን ቀምሮ እነዚህን ሃሳቦች ደግሞና ደጋግሞ በማሰማት ህብረተሰቡ እንዲያዉቃቸዉና እንዲያምንባቸዉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ህብረተሰቡ በተለያዩ ሰዎችና አካላት ተደጋግሞ የሚተላለፍለትን መልዕክት በሚሰማ ጊዜ ይህንን ሊቀበል የሚችልበት እድል ሰፊ ነዉ፡፡ በመልዕቱ መሰረት ወደ ተግባር ሊገባ የሚችልበት ዕድልም አብሮ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ ለሰፊ ዉይይትና ስልጠና ጊዜ የሌለዉ ቢሆንም የራሱን ህይወት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በአጭሩ ተቀርፀዉ የቀረቡለት መልዕክቶች በትክክል እንዲደርሱት ከተደረገ ህብረተሰብን በእነዚህ አቅጣጫዎች ማሰብና ተግባራቱንም መምራት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በመልዕክቱ መስራተተ ህብረተሰቡን በሰፊዉ አንቀሳቅሶ ለዉጥ ለማምጣት ልዩ ተፈላጊነት ያለዉ የኮምዩኒኬሽን ስራዎች ማስፈፀሚያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

መልዕክቶች አጫጭርና ከፍተኛ ተፅዕኖ አድራጊ የህዝብ ግንኙነት መሳሪያዎች በመሆናቸዉ ለይዘታቸዉ ትክክለኛነት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባዋል፡፡ በአለማችን በጣም ብዙ አገሮችና የፖለቲካ ሀይሎች በዚህ አሰራር ተጠቅመዉ የሚፈልጉትን አስተሳሰብ የማስረፅ ችሎታ እንደነበራቸዉ አሳይተዋል፡፡ ይልቁንም አንዳንድ ጊዜ በመልዕክት መስራትን ኋላቀርና አፍራሽ ሃይሎችም የራሳቸዉን አላማ ለማራመድ የሚጠቀሙበት ስለነበር እዚህን ወገኖች ከተሳሳተ ዓላማቸዉ የሚመነጭ የተሳሳተ መልዕክት ቀርፀዉ በአለም ላይ ከባድ ጥፋት አስከማድረስ ደርሰዋል፡፡ ለምሳሌ በጀርመን ባለፈዉ ምዕተ ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ብቅ ያለዉ የናዚ ሃይል የጀርመንን ህዝብ አስተሳሰብ ለመበረዝ መልዕክትን እንደ ዋነኛ መሳሪያ በዉጤታማነት ሊጠቀምበት በመቻሉ ፋሺዝም በጀርመን ከመንሰራፋት አልፎ በአለም ላይ ከባድ ጥፋት እስከማስከተል ደረሷል፡፡ በመሆኑም አፍራሽ መልዕክት አፍራሽ ውጤት ሲያከትል፣ ገንቢ መልዕክት ደግሞ ገንቢ ዉጤት ሊያከትል እንደሚቸል በመገንዘብ ለመልዕክቶች ገንቢ ይዘት ተፈለጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡

መልዕክቶች አጭርና ግልፅ ሆነዉ ብቻ ሳይሆን ይዘታቸዉም ትክክለኛ ሆነዉ ከተቀረፁ በኋላ ህብረተሰቡ ያዉቃቸዉ ዘንድ በልዩ ልዩ አግባቦች ተደጋግመው ሊቀርቡለትና እንዲሰማቸው ሊደረግ ይገባል፡፡ አንድ መልዕክት አንዴ ብቻ ተላልፎ በሁሉም ሳይደመጥ ሊቀር ይችላል፡፡ ያዳመጡትም ሰዎች በደንብ ሊያጣጥሙት ይችላሉ፡፡ስለዚህም ተደጋግሞ ካልተነገረ ተፅዕኖዉ አነስኛ ሊሆን ወይም ከእነ አካቴዉ ተፅዕኖ ሳይኖረዉ ሊቀር ይችላል፡፡ መልዕክት ከፍተኛ የተፅዕኖ ሃይል የሚኖረዉ ተደጋግሞ ሲነገር በመሆኑ በተለያዩ አግባቦች መልዕከቶችን ደግሞ ደጋግሞ ማስተላለፍና ወደ ተፈላጊዉ የህብረተሰብ ክፍል እንዲደርስ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡መልዕክቶች በሚደጋገሙበት ጊዜ የማሰልቸት ባህሪ እንደሚኖራቸዉ ቢታወቅም በአንድ በኩል መልዕክቱን ፈጠራ በተመላበት መንገድ በመደጋገም፣ በሌላ በኩል አስፈላጊ ሆኖ ከተተገኘም እንዳለ በመደጋገም ማሰማት አማራጭ የሌለዉ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ይህ ሲሆን ህብረተሰቡ መልዕክቱ ከያዘዉ ፅንሰ ሃሳብ ጋር በቅርብና በተደጋጋሚ ሊተዋወቅ ዕድል ያገኛል ፡፡ በዚያዉም ልክ ሃሳቡን የራሱ የሚያደርግበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

መልዕክት በተደጋጋሚ የሚተላለፈዉ ዞሮ ዞሮ ህዝቡን ወደ አንድ ድርጊት ወይም የለዉጥ ተግባር ለመምራት ነዉ፡፡ መልዕክቱ በበቂ አኳኋን ከተላለፈ ዉሎ አድሮ ህብረተሰቡ ለድርጊት መነሳሳቱ አይቀርም፡፡ ስለሆነም መልዕክቱን ተከትሎ ወደ ስራ ይገባል፡፡ ይህም አንደገና ለሌላ የህዝብ ግንኙነት ስራ ጥሩ መሰረት ሆኖ ያገለግላል፡፡ ህዝቡ በተነገረው መልዕክት መሰረት ወደ ተግባር ሲገባ በአስተሳሰብ ደረጃ ብቻ ሳይወሰን በድርጊትም ለዉጥን መቀበል እንደቻለ ያሳያል፡፡ ለዉጥን በተግባር የሚቀበል ህረተሰብ ደግሞ እዚያዉ ሳለ አዳዲሰ የለዉጥ ሃሳቦችን ለመስማትና የራሱ ለማድረግ ይችላል፡፡ በመሆኑም በመልዕክት በምንሰራበት ጊዜ ያቀረበለትን ሃሳብ ተቀብሎ ወደ ተግባር የተሸጋገረዉን ህዝብ ለላቀ ተግባርና የአስተሳሰብ እድገት ለማብቃት የሚያስችለን ተጨማሪ የኮሚዩኒኬሽን ስራ ልንሰራበት ይገባናል፡፡ ይህም ሲሆን ዉጤታማ ሊሆን የሚቻለዉ በመለዕክቶች አማካኝነት የፈጠርነዉን ግልፅነት መነሳሳት እንዲሁም ህዝቡ ወደ ተግባር ሲገባ ያሳየዉን ተነሳሽነትና በአሰተሳሰብ ደረጃ ያልተሻገራቸዉን ጉዳዮች ለማወቅ የሚያስችል ተጨማሪ የህዝብ አስተያየት በማሰባሰብ ነዉ፡፡ የህዝብ አስተያየት ቋሚና ለዘላለም የተሰጠ ጉዳይ ባለመሆኑ ሊዳብርም ሊያሽቆለቁልም የሚችል ጉዳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም በመልዕክቶች ስንሰራ ህዝቡ ባስተላለፍንለት መልዕክት ዙሪያ የፈጠረዉን ስሜት በቅርብ ተከታትሎ እንደ አስፈላጊነቱ በመልዕክቱ ላይ ትንሽም ሆነ መሰረታዊ ለዉጥ ማድረግ ይገባል፡፡ መልዕክቶች የሚፈለጉት በአንድ ወቅት የተለየን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡን ወደ ተግባር ለማምራት ነው፡፡ ተግባሩ በተሳካ ሁኔታ ከተፈፀመ አዲስ እውነታ ይፈጠራል፡፡ይህ እዉነታ ካለፈዉ ጋር በተወሰነ መልኩ የሚመሳሰል፣ በተወሰን ደረጃ ደግሞ የሚለያይ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ነባር መልዕክቶችን መቀየር ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ይህ የሚያመለክተዉ መልዕክቶች አንዱ ከተቀረፁ በኋላ እሰከ ዘላለም የሚቆዩ እንዳልሆኑ ይልቁኑ የራሳቸዉ የዕድሜ ቆይታ ያላቸዉ ጉዳዮች እንደሆኑ ነዉ፡፡ ስለዚህም ሁሌም ቢሆን በመልዕክቶች በመስራት የመጣዉን ለዉጥ በመገምገም አዲስ መድረክ የሚጠይቃቸዉን አዳዲሰ መልዕክቶች ለመቅረፅ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡”

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.