ዛሬን በኢትዮጵያ ….

እለተ ቀኑ ጅንጉርጉር ነበር …. የተዘጋም …. የተከፈተም::

አንድ ግልፅ መልእክት ግን ተላልፏል …. ማንም ወጥቶ ተላለቁ ስላለ ኢትዮጵያውያን አንተራረድም::

የዛሬው እውነታ ያመላከተው ኢህአዴግ ከህዝቡ ምን ያህል እንደራቀ ነው:: ከሚኒሶታ በአንድ Laptop የሚታመስ መንግስት እራሱን በቅጡ መፈተሽ አለበት::

የኦቦ ለማ መንግስትም ከተራ ልወደድ ባይነት አካሄድ (Populist) ወጥቶ ወደ ሰከነና አርቆ አሳቢ መንገድ ቢመጣ ይሻለዋል:: የድርጅቱ official Facebook ገፅም ቀኑን ሙሉ የፍየል ገበያ እያሳየ ሱቅ ተከፍቷል ሲል ከሚውል ይልቅ ወደ ስክነት ወርዶ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማቅረብ አለበት::

መቼስ እንደዘንድሮ ኢህአዴግ አስቂኝ  የለም:: በትግሉ ዘመን ህዝባዊነትን እንደሰነቁ የተሰውት ታጋዮች ምን ያህል የታደሉ ነበር:: እንኳንም ዛሬን አላዩ!!

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!!!

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.