የህግ የበላይነት በክልል ሱማሌም ሊተገበር ይገባል!

(EthiopiaFirst.com) – በተወሰኑ የኦሮምያና ኢትዮ ሱማሌ አካባቢዎች ተከስተው በነበሩ ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዙርያ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ እየሰማን እንገኛለን:: ይህም ይበል ይቀጥል የሚያስብል ነው::

የፀጥታ ም/ቤቱ የጀመረውን ስራ “የንጉስ ዶሮ” ነኝና ማንም እኔን አይነካኝም የሚሉት ወንጀለኞችን በሙሉ የሚጎተት መሆን አለበት::

ሰሞኑን የመንግስት ኮምንኬሽን ሃላፊ እንደተናገሩት የፌደራል መንግስቱ የፀጥታ ሃይሎች ክልል ሱማሌ የሚገኙ ወንጀለኞችን ለመያዝ የክልሉ አመራሮች እንቅፋት ሆነውባቸዋል:: የአንድ መንግስት ቁጥር አንድ ሃላፊነቱ የህግ የበላይነት ማስከበር በመሆኑ ይህንን ማድረግ እውነትም ካቃተው መንግስት ተብሎ የመጠራት መብቱንም ያጣል::

በሀገሪቷ ረጅም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችንን በግፍ ያፈናቀለው የክልል ሱማሌው አብዲና ጀሌዎቹም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይገባም::

የህግ የበላይነት እንዳይከበር እንቅፋት የሚሆኑ በሙሉ (ማንም ይሁኑ ማን) እራሳቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው::

Leave A Reply

Your email address will not be published.