የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሥርዓት-ትምህርት ሊቀረጽ ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳለው ሥርዓተ-ትምህርቱ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በልማታዊ መንግስት ንድፈ ሃሳብ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያጎለብቱ ያለመ ነው ፡፡

የተለያዩ የአመራር ስልጠናዎችን የሚሰጠው የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ንድፈ ሀሣብን በስርዓተ-ትምህርቱ ውስጥ እንዲቀረፅ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በልማታ ዴሞክራሲ መንግስት ንድፈ ሀሳብ ላይ የመንግስት ሹመኞች እና የህብረተሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ እንደሆነ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡በሌላ በኩል ከጊዜ ወደ ጊዜ የአመለካከት ለውጥ እየተፈጠረ መጥቷል የሚሉ ምሁራን ሲኖሩ የበለጠ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ግንዛቤ በሀገሪቱ እንዲጎለብት ተጨማሪ ስራዎች አስፈላጊ አንደሆኑ ይጠቅሳል፡፡

ለዚህም አሁን ላይ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ንድፈ ሀሣብ ስርዓተ-ትምህርት ውስጥ መካተት አለበት የሚል ደረጃ ላይ እንደተደረሰ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ እየገለፀ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.