የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ሚንስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ከኳታሩ ምክትል ጠ/ሚ ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ

(EBC)- የኳታር  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ቢን  አብዱላሂ ቢን ዘይድ  አል መሃመድ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች  ሚኒስትር  ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ጋር በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩት በዋና ከተማዋ በዶሃ ነው፡፡

ባለስልጣናቱ የሁለቱን አገራት ግንኑኝነት ለማጠናከር በሚችሉ  የተለያዩ ጉዳች ላይ መወያየታቸውን ገልፍ ታይምስ ዘግቧል፡፡

በውይይቱ ላይ በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር  ምስጋኑ አርጋ ና ሌሎች ባለስልጣናት ተሳትፈዋል ፡፡

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከኳታሩ አልጀዚራ ጋር ተባብሮ ለመስራት የሚያስቸለውን የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ተባብሮ ለመስራት  ወደቦታው ያቀናውን ቡድን በመምራትም ከአልጀዚራ የስራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸውንም   ኢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.