የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ እየተከበረ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው።

ትናንት በሀዋሳ ከተማ መከበር የጀመረው የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል ዛሬም በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ደምቆ እየተከበረ ይገኛል።

በሲዳማ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ “የቄጣላ” ጨዋታና የፈረስ ጉግስን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያከናውናሉ።

በዓሉ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።

የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ”ፊቼ ጨምባላላ” በዓል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት በ2008 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ መመዝገቡ የሚታወስ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.