የስነ ምድር ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ጥንታዊት ከተማ አግኝተናል አሉ

በአስረኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የተቆረቆረች እና የተረሳች የተባለችው ከተማ በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ሀርላ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ማግኘታቸውን የስነ ምድር ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

እንደ BBC ዘገባ በግብፅ፣ ህንድ እና ቻይናውያን የተሰሩ የእደ ጥበብ ውጤቶች በዚሁ በሀርላ ግዛት ተገኝቷል፡፡

ተመራማሪዎቹ በ12ኛው ክፍለ ዘመን የተመሰረተ ጥንታዊ መስጂድ ማግኘታቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡

ግኝቱ በአፍሪካ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ታሪካዊ ትስስርን ያሳያል ብለዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.