የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአገራችን እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን አደነቀ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አልሁሴን በምክር ቤቱ 38ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአገራችን እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን አድንቀዋል፡፡

በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተነሳሽነት በአገራችን ለውጦች መምምጣታቸውን በመጠቆም፣ የህግ የበላይነት ከማስፈን፣ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች መርሆዎችን ከማስከበር፣ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ፣ የመሰብሰብ መብት እና የሲቪክ ማህበራት ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳት እና የእስረኞች መፍታት ሊደነቅ እንደሚገባው በመግለጽ የሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ሂደቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ እገዛ የሚያደርጉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነር ዘይድ በቅርቡ በአገራችን ጉብኝት በማድረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.