የትግራይ ክልል ምክር ቤት የ574 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

(ኤፍ ቢ ሲ)- የትግራይ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችንና ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ በዛሬው እለት አጠናቋል።

ምክር ቤቱ ሶስት የቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት ሲያጸድቅ ለአንድ የቢሮ ሃላፊ ደግሞ እውቅና ሰጥቷል።

በዚሁ መሰረት፦

  • አቶ አማኑኤል አሰፋ- የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ
  • አቶ ነጋ አሰፋ- የክልሉ የወጣቶች ጉዳይና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
  • አቶ ረዳኢ ሃለፎም የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ ባለፈም የዶክተር አትንኩት መዝገቡን ለክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊነት እውቅና ሰጥቷል።

እንደዚሁም ምክር ቤቱ 574 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀትም በዛሬው ማጠናቀቂያው ላይ አፅድቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.