የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና በትግርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና ትግርኛ ቋነቅ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የግዕዝና የትግርኛ ቋንቋን ስርዓተ ትምህርት ለማጽደቅ የሚያስችል መድረክ ተዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይም ዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርሃ ግብሩን በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

መርሃ ግብሩ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሦስት ዓመታት የሚሰጥ ነው ተብሏል።

በቀጣይም ሁለተኛ ዲግሪ ለመጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የመርሃ ግብሩ መጀመር በአክሱም ከተማና ዙሪያ የሚገኙ ታሪካዊ ምርምሮችና ጽሁፎች በቀላሉ ለመተርጎምና ጥቅም ላይ ለማዋል ይረዳል ብሏል፡፡

በመድረኩ ከአዲስ አበባ፣ ከመቐለና ከአዲግራት የኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ100 በላይ ምሁራን የተሳተፉ ሲሆን፥ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.