የአዲስ አበባ የኦህዴድ አባላት ድርጅታዊ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

(ኤፍ.ቢ.ሲ)- የአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 7ኛ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከጥቅምት 27 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ኮንፍረንስ ላይ የድርጅቱ አመራሮችን ጨምሮ 940 አባላት በመሳተፍ ላይ ግኛሉ።

ኮንፍረንሱ ከጥልቅ ተሃድሶ በኋላ ምን ተሰራ፣ ምንስ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች አሉ እንዲሁም ድርጅቱን ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ሲመክር መቆየቱን የአዲስ አበባ ኦህዴድ ኮሚቴ ሃላፊ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ተናግረዋል።

የኮንፍረንሱ አባላት በ11 ቡድኖች ተከፍለው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ የቆዩ ሲሆን፥ የተለያዩ ጥያቄዎችንም አነስተዋል።

ለተነሱ ጥያቄዎችም የኦህዴድ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አበይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ መልስ በመስጠት የማጠቃለያ ውይይት በመካሄድ ላይ ግኛል።

በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማእከል ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ድርጅታዊ ኮንፍረንሱ ከሰዓት በኋላ አባላቱ በሚያወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.