የአገሪቱ የውጭ ንግድ አሽቆልቁሏል ተባለ

4 ነጥብ 2 በመቶ ቅናሽ ባደረገው የወጭ ንግድ፣ የግብርና ምርቶች ዋጋ መውረድ እንደ አንድ ምክንያት ተገልጿል፡፡

ያየሰው ሽመልስ

ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ 70 በመቶ የሚሆነው የግብርና ምርቶች ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡

መንግስት በ2ኛው የልማት ዘመን ወደማምረቻው ዘርፍ ለመሸጋገር ባቀረበው እቅድ የውጭ ንግድን ማስፋፋት የሚለው ቀዳሚ አጀንዳ ነው፡፡ ከ 1 ዓመት በላይ የተሻገረው ይኼ ዕቅድ ሲታይ ግን መጠኑ ከፍ ያለ ቅናሽ የታየበት ነው፡፡ በተለይም የውጪ ንግድ 4 ነጥብ 2 በመቶ ማሽቆልቆሉን ጠ/ሚሩ ተናግረዋል፡፡

ለውጭ ንግዱ መቀነስ ምክንያት ሆኖ የተጠቀሰው የግብርና ምርቶች ዓላማቀፋዊ ዋጋ ማሽቆልቆል ነው፡፡

ከግብርና ምርቶች በዘለለ ኢትዮጵያ ከማዕድናትና ከቁም እንስሳትም የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች፡፡ ይሁን እንጂ ከእነዚህ ምርቶች በህገ-ወጥ ነጋዴዎች የተያዙ በመሆናቸው መንግስት የሚፈልገውን ውጤት ማግኘት አልቻለም፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.