የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበሮችን በጋራ ስለማልማት የሚመክር ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

ለ18ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ጉባኤ የትግራይዋ መዲና መቀሌ ታስተናግደዋለች ተብሏል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ በድንብር አካባቢ ስለሚካሄዱ የንግድ ልውውጦች የድንበር ግብርና ስራዎች እና ስለ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ውይይት ይደረጋል፡፡

በጉባኤው ላይ ከሱዳን በኩል የጋዳሬፍ ፣ የብሉናይል፣ የሴናርና የከሰላ ግዛቶች ይሳተፋሉ፡፡ ከኢትዮጵያ ደግሞ ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል በውይይቱ ላይ ይገኛሉ ሲል ሱዳን ትራቡን ጽፏል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.