የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ ተሾመለት

(EBC)- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ ተሾመለት የማህብሩ ስራ አስኪያጅ ሆና የተሰየመችው ወጣቷ ቤዛ ተስፋዬ ናት፡፡

በአፍሪካ የፔስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቁልፍ ሚና ካለቸው 13 ሴቶች አንዷ  የሆነችውና ስፔስ ጀነሬሽን የአፍሪካ አማካሪ  ምክር ቤት አስተባባሪ የነበረችው ቤዛ የኢትዮጵያን ስፔስ ስፔስ  ሳይንስ ሶሳይቲ እንድትመራ እድሉ ተሰጥቷታል፡፡

በአለም አቀፍ ጥናቶችና ግንኙነት ዘርፍ የመጀመሪያ ድግሪ ያት ቤዛ በኮምፒውተር ሳይንስ ደግሞ እስከ ሁለተኛ ድግሪ ድረስ ገፍታለች፡፡

በማህበሩ ውስጥ ከፍተኛውን የኃላፊነት ቦታ ያገኘችው ቤዛ እ.ኤ.አ ከ2004 ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማህበር አባል ሆና ስታገለግል የቆየች መሆኗን በህዋ ላይ ያተኮረ መረጃ የሚያጠናክረው አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡

በመንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትነት 47 አባላትን ይዞ የተመሰረተው ማህብሩ በአሁኑ ጊዜ ከ10ሺ በላይ አበላትን አፍርቷል፡፡

ዓለማውም ኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ በመዋል ለሁለንተናዊ የእድገት አማራጮቿ ጥቅም ላይ እንድታውልና ለስነ ፈለክ ጥናት ደግሞ የራሷን ሚና እንድትወጣ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.