የኢትዮጵያ አየር መንገድ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ መረጠ

(ኢዜአ)- አየር መንገዱ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት በሴቶች የአቪዬሽን ባለሙያዎች ብቻ የሚመራ በረራ ወደ ላቲን አሜሪካዋ አርጀንቲና ዋና መዲና ቦነስ አይረስ አድርጓል።

አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ የሶሰት ጊዜ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋን አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አምባሳደሩ አድርጎ መርጧታል።

የአፍሪካዊያን ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር አየር መንገድ ወደ አርጀንቲና ያደረገው በረራ በአሜሪካ አህጉር ስድስተኛው መዳረሻ ሆኗል።

በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ታሪክ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአንድ የኦሎምፒክ ውድድር በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር በእድሜ ትንሿ ውድድሩን ያሸነፈች አትሌት ናት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ሲሆን የአየር መንገድ ደረጃ አውጪ በሆነው ስካይ ትራክስ የአራት ኮከብ ደረጃ እንደተሰጠው ይታወቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.