የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ክንፉ ላይ መጠነኛ ጉዳት አጋጠመው

(EBC)- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን በምድር ላይ እንዳለ ከሌላ የህንድ ኤርባስ ኤ320 አውሮፕላን ጋር ክንፉ ጫፍ አካባቢ ላይ በመጋጨቱ መጠነኛ ጉዳት ደረሰበት::

አውሮፕላኑ ጉዳቱ ያጋጠመው በህንድ ደይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በሚዘጋጅበት ወቅት ነው፡፡

አውሮፕላኑ የሚያስፈልገው ጥገና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የደህንነት መርህ መሰረት እየተደረገለት እንደሚገኝም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ባጋጠመው መጠነኛ አደጋ መንገደኞቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ምቾቱና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.