የኢትዮጵያ የቀጣዮቹ 15 አመታት የጥጥ ልማት እቅድ በአዲሱ በጀት አመት መተግበር ይጀምራል ተባለ

እቅዱን ለማዘጋጀት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር አማካሪ ድርጅቶች ሲካሄድ የነበረው ጥናት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

የሀገር ውስጥ የጥጥ ምርት በማሳደደግ ከውጭ የሚገባውን በቀጣይ 15 አመታት የሚተገበበረውን የጥጥ ልማት ማስቀረት ለእቅዱ ዋና ትኩረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለኢ.ዜ/አ እንደገለፀው እቅዶቹ ከሚቀጥሉት በጀት አመት ጀምሮ ይተገበራል ተብሏል፡፡

እቅዱን ለማዘጋጀት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር አማካሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመለየት ጥናት ሲካሄድ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለመጠቀም እና መሰል ችግሮችን በመፍታት ተወዳዳሪነት እና የገበያ አቅርቦትን ለማሳደግ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ከ100 እስከ 150 ሺህ ቶን ጥጥ ማምረት የሚያስችል 100 ሺ ሄክታር መሬት ቢኖራትም እየተመረተ ያለው ግ ከ 60 እስከ 70 ሺህ ቶን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.