የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክስዮን ማህበር መስተጓጎል ገጥሞኛል አለ

(ENN TV)- የኢትዮጅቡቲ ምድር ባቡር አክስዮን ማህበር ስራ በጀመረባቸው ጥቂት ቀናት መስተጓጎል ገጥሞኛል አለ

የሁለቱ አገራት መንገደኞች በመዳረሻዎቻቸው ላይ ብቻ ፍተሻ እንዲደረግ የተስማሙ ቢሆንም ወሰን ላይ መንገደኞችን በማስቆም ከሰሞኑ ፍተሻ ተደርጓል፡፡

ስምምነቱን በተግባር ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በድንበር ደህንነትና ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ ሁለቱ አገራት በጅቡቲ መክረዋል፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ አምስት ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው ፕሮጀክቱ በማቋረጫ አካባቢዎች ችግር ገጥሞኛል አለ፡፡

የኢትዮጵያ የትኬት ጣቢያዎች ከስርአት በተያያዘ መስተጓጎል እንደነበር የፕሮጀክቱ ዋና አስፈፃሚ ጥላሁን ሳርካ ተናግረዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.